Skip to main content
aply

የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችል ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድልን ሁሉም ወጣቶች እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ። (ሆሳዕና፣ ታህሳስ 17/2017) ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትልና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻቤቦ በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የኮዲንግ ሥልጠና ሂደትን ተመልክተዋል። በዞኑ የኮዲንግ ሥልጠና ሂደት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን አቶ ከበደ ተናግረው፤ የኮዲንግ…

የኮዲንግ ሥልጠና ሂደትን በጉራጌ ዞን አበረታች ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። (ሆሳዕና፣ ታህሳስ 16/2017) ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ አገና ከተማ አስተዳደር የኮዲንግ ሥልጠና ሂደትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ቢሮ ኃላፊው የኮዲንግ ሥልጠና ሂደት በጉራጌ ዞን አበረታች ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠናውን ሂደት ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ነው…

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ቀጥሏል፡፡ ወራቤ፣ ታህሳስ 2017 ዓ/ም በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎችን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ቼክሊስት በማዘጋጀት እና ሁለተኛ የድጋፍ ቡድን በማደራጀት ስምሪት ሰጠ…

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ጀመረ፡፡ ወራቤ፣ ታህሳስ 2017 ዓ/ም በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎችን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ቼክሊስት በማዘጋጀት እና የድጋፍ ቡድን በማደራጀት ስምሪት መሰጠቱን ተጠቆመ። የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በዋናነት በየደረጃው…

በክልሉ ትኩረት በተሰጣቸው የልማት ዘርፎች የምርት ጥራትና ምርታማነትን የሚያጎለብቱ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ ስራዎችን በማከናወን ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን አምርቶ መተግበር የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመ:- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት መስራት የሚያስችል መግባቢያ ሰነድ መፈረም መቻላቸው ተሰማ፡፡ በመድረኩ የተገኙት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ…

ተቋማት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በብቃት እንዲጠቀሙ የሚያስችል አቅም ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለጸ። ቢሮዉ ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ ባለሙያዎች በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ጥገናና እድሳት ላይ ያዘጋጀው የተግባር አቅም ግንባታ ስልጠና በወራቤ ከተማ እየተሰጠ ነዉ። ስልጠናውን ያስጀመሩት የቢሮው ምክትልና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና…

ህዳር 6/2017 ዓ.ም በሳይንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ከኢንተርፕሪነር ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት ለዞን፣ ለልዩ ወረዳ አመራሮችና ለባለድርሻ አካላት ለተከታታይ 3 ቀናት በወልቂጤ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን…

ህዳር 4/2017 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢንተርፕሪነር ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት ለዞንና ለልዩ ወረዳ አመራሮችና ለባለድርሻ አካላት ስልጠና በወልቂጤ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል። ስልጠናው በፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕ እና ኢኖቬሽን ኢኮሲስተምና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ አሰጣጥና አስተዳደር ዙሪያ ለ3 ተከታታይ ቀናት በመስጠት ላይ ነው። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ…

ኢትዮ ኮደርስ በክልሉ በሥራ ዕድል ፈጠራ የሚኖረው አበርክቶ ጉልህ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ ተናገሩ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የሀገሪቱን ዲጂታል ክህሎት ከፍ ለማድረግ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ዲጂታል ኮደርስ የሚኖረው አበርክቶ ጉልህ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ አንተነህ ይህን የተናገሩት የዋን- ዋሽ፣ የኮ-ዋሽ ፕሮግራም…

በሀገሪቱ እየተካሔደ ያለውን የእድገት ጉዞ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሳይንስ ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ ወራቤ፣ጥቅምት 22/2017 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊስ እና የኢኖቬሽን አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጥቷል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደገለጹት የሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊስ እና የኢኖቬሽን አስተዳደር…