
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ የሁለትዮሽን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል። ምክሩን ያካሂዱት የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያና ቻይና የጋራ ስትራቴጂካዊ አላማዎቻችንን ከግብ ለማድረስ እና የኢትዮጵያና የቻይና ቤተሰብ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆን ከፈለግን እንዲህ ያለው ከፍተኛ ትብብር አስፈላጊ ነው ብለዋል። ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሀገራትም የሚጠቅሙ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለማበረታታት ከቻይና ጋር ተቀራርበን ለመሥራት ቁርጠኞች ነን ብለዋል። በዲጂታል ኢኮኖሚ እና ፈጠራ የFOCAC አጀንዳ አፈፃፀም ውስጥ ዋና ምሳሌ መሆን እንፈልጋለን ያሉት ሚኒስትሩ የበለፀገ እና በዲጂታል የነቃ ማህበረሰብን ለማራመድ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል። የቻይና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዪን ሄጁን (Mr. Yin Hejun) ቻይና በሁለቱ ሀገራት ያለውን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል። በጋራ የምርምር ውጥኖች እና አካዳሚክ ትብብር፣ እንደ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የጤና ቀውሶች እና ዘላቂ ልማት ያሉ አሳሳቢ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የጋራ እውቀታችንን ማሰባሰብ እንደመገባ በምክክሩ ላይ ተነስቷል። በFOCAC 2024 የመሪዎች ጉባኤ ላይ የታቀዱትን አስር የአጋርነት የድርጊት መርሃ ግብሮችን በተግባር ላይ በማዋል እንደ ንግድ፣ የኢንዱስትሪ ሰንሰለት ትብብር፣ አረንጓዴ ልማት እና የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ፣ ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ ከሳይበር ደህንነት እና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር የተያያዙ ጥረቶችን ለማራመድ በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቁሟል።