CebositAdmin
Fri, 09/26/2025 - 16:38

የ2018_በጀት_ዓመት_የ1ኛ_ሩብ ዓመት የክትትልና ድጋፍ ስራ መስራቱ ተሰማ። የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በዞንና በልዩ ወረዳ ሳኢቴ መዋቅሮች የ2018_በጀት_ዓመት_የ1ኛ_ሩብ ዓመት ተግባራት አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ ቡድን በማሰማራት መገምገም ተቻለ። በክትትልና ድጋፍ ስራ የታዩ ዋና ዋና ተግባራት:- የዝግጅት ምዕራፍ የተመራበትን አግባብ; በየመዋቅሩና ተቋማት የዲጂታላይዜሽን ትግበራ; የኢትዮ ኮደርስ እና የስፔስና ጂኦ ስፓሻል ስልጠናዎች; የኢኖቬሽን/ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ ስራዎች; የክረምት የ90 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀም; የሪፎርም ትግበራና እና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም እንዲሁም ሌሎችንም ተግባራት በማካተት በጥንካሬ የተፈፀሙትን አጠናክሮ በማስቀጠል በሂደቱ በውስንነት የተገመገሙትን የሚያርም ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ተችሏል።