Skip to main content

በኢኮቴ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ

የኢኮቴ የግል ስራ ፈጠራ ማዕከላት አገልግሎትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

  • በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የግሉን ዘርፍ ተሳታፊነት ማጎልበትና ውጤታማነቱን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን፣
  • በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማቋቋም፣ ማደራጀትና ማስፋፋት፣
  • በኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የግል ስራ ፈጣሪዎችን በደንብና ስርዓት መሰረት እንዲደራጁ ማድረግ፣
  • በኢንኩቤሽን ማዕከላት ለተደራጁ ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩላቸውና የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
  • የተደራጁ ማዕከላት ራሳቸውን ችለው በግላቸው መንቀሳቀስ እንዲችሉ ቀጣይነት ያለው ማብቃትና የክትትል ስራዎችን መስራት፣
  • አዳዲስ ኢንኩቤቶችን ይመለምላል መሠረታዊ የኢንተርፐርነርሺፕ፤ የቢዝነስ እቅድ አዘገጃጀትና የሂሳብ አያያዝ ሥልጠናዎችንና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይሰጣል
  • የእያንዳንዱን ኢንኩቤት ድርጅት የቢዝነስ ዕቅድ ይገመግማል ፣ግብረመልስ ይሰጣል፣ ያደራጃል፣ ያበቃል፡፡
  • በማዕከል ውስጥ ያሉ ንብረቶችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለኢንኩቤቶች ያከፋፍላል የመስሪያ ቦታን በኪራይ ይሰጣል፡፡
  • በመደበኛ ሁኔታ የኮቺንግና ሞንተሪንግ አገልግሎት ለኢንኩቤቶች ይሰጣል
  • በየወቅቱ የኢንኩቤቶች የሥራ አፈጻጸምን ይገመግማል፣ አስተያየት ይሰጣል፣ እርምጃ ይወስዳል፣ ደካማና ጠንካራዎችን ይለያል፡፡
  • የገበያ ትስስር ይፈጥራል፣ የተገኙ የገበያ ዕድሎችን በውድድር ወይም ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ኢንኩቤቶች እንዲተቀሙ ያደርጋል፡፡
  • ኢንኩቤቲዎች በመንግስት ደንብ መሰረት በህግ እንዲቋቋሙ ያደርጋል
  • የኢንኩቤቶችን ክፍተት በመለየት አስፈላጊውን ሥልጠናና የአቅም ግንባታ ድጋፍ  እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ብቁ የሆኑ ኢንኩቤት ድርጅቶችን በመለየት ያስመርቃል በገበያ ውስጥ ገብተው ተወዳዳሪና ብቁ ባለሃብት እንዲሆኑ ያግዛል፡