የቢሮዉ ኃላፊ መልዕክት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ቢሮ
አቶ ሰላሙ አመዶ ዋጨንጎ የቢሮው ሀላፊ መልዕክት
የቢሮው ሀላፊ መልዕክት
ሳይንስና ኢንፎርመሽን ቴክኖሎጂ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከምንም በላይ መሆኑን ዛሬ ላይ የስልጣኔ ጫፍ የደረሱ፣ የበለፀጉና የዓለማችን ሃያላን ተብለው የሚጠሩ አገሮች ምሥክሮች ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ መንግስት የሀገራችን ሕዝብ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆንና የቴክኖሎጂው ሽግግር ከጫፍ እንዲደርስ ተግቶ በመሥራቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀላል የማይባል የሀገራችን ሕዝብ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ችሏል፡፡ ለዚህም ማሳያ መሆን የሚችሉ በርካታ ተግባራትን መጥቀስ የሚቻል ሲሆን በክልላችን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች ጋር በመሆን በአያሌ የገጠር ቀበሌያትና ወረዳዎች የገጠሩ ሕብረተሰብ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከሌሎች የመረጃ ምንጮች የሚፈልጓቸውን መረጃዎች በተለያዩ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች አማካይነት ማግኘት እንዲችሉ የማህበረሰብ መረጃ ማዕከላትን አቋቁሞ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሽቦ አልባ ስልኮችም በብዙ የገጠር ቀበሌያት በቢሮውና አግባብነት ባላቸው ተቋማት በኩል የተሠራጩ ሲሆን እስኩል ኔትና ወረዳ ኔቶችም እንዲሁ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልል ማዕከል፣ በዞኖች፤ በልዩ ወረዳዎች፤ በወረዳዎችና በከተማ አስተዳደሮች የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ደረጃ በደረጃ እየተዘረጋ ያለ ሲሆን በዋናነት የመንግስት መረጃ ሥርዓት የማሳለጥ፣ የቪዲዮ ኮንፍረንስ አገልግሎት በመስጠት ፈጣን የሆነ መረጃ እንዲዳረስ የማድረግና የማህበረሰብ መረጃና ሬድዮ አገልግሎት በመስጠት በርካታ ወጣቶችን በማደራጀትና በማሰልጠን ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል፡፡ ባለፉት ዓመታት በኢኮቴ ዘርፍ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ተመራቂዎችን በማህበር በማደራጀት የተለያዩ ድጋፎችን ማለትም ስልጠና፣ የገበያ ማፈላለግና የማማከር አገልግሎት በመስጠት የግል ካምፓኒ ፈጥረው ወደ ንግድ ዓለም እንዲገቡ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቢሮውን ዌብ ሳይት በማልማት እና የፌስቡክ ገጽ በመክፈት እንዲሁም የተለያዩ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በተቋማችን አጠቃላይ አፈጻጸምና ሁኔታ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እተከናወነ ይገኛል፡፡
የሚሰጡ አገለግሎቶች
ወቅታዊ ዜናዎች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 40ሺ ዜጎች በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ተጠቃሚ መሆናቸው ተመላከተ በክልሉ በ5ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገብ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ…

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በኢትዯጵያ ህዴሴ ግድብ ቦንድ ግዥ ላይ በትኩረት ማሳተፉን አስታወቃ።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) የማህበራዊ ክላስተር ሴክተሮች የዕቅድ አፈጻጸም በጽ/ቤታቸው እየገመገሙ ነው ሆሳዕና፣መጋቢት 15፣2017፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የማህበራዊ ክላስተር መስሪያ ቤቶች አመራሮች እና ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የክላስተሩ…

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ8 ወራት ዋና ዋና ተግባር አፈፃፀም በማነጅመንት ገመገመ። በየዘርፉ የእስካሁን አፈፃፀም ከዕቅድ አኳያ በጥንካሬ፣ መሻሻል በሚገባቸውና ቀጣይ ትኪረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ሪፖርት ቀርቦ መገምገም ተችሏል። በመድረኩ የተገኙት የቢሮ ኋላፊ አቶ ሠላሙ አማዶ…

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ እና የክልሉ ጤና ቢሮ እንደ ተቋም የመረጃ ስርዓቱን ለማዘመን እና ጊዜውን የዋጀ መረጃን ለማደራጀት ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ እና ከጉራጌ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመቀናጀት የሲስተም ልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ…

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የድረ ገፅ ማስተዳደርና የሳይበር ደህንነት ቴክኒካል ስልጠና ለክልሉ ፍትህ ቢሮ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ። የካቲት 13/2017 ዓ.ም ቢሮው ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የድረ-ገጽ ልማት…
ተልዕኮ
ለክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋት ክልላዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡
ራዕይ
“በ2030 በክልላችን ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣ የማልማት፤ የመፍጠር፣ የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት”
እሴቶች
በጎ ህሊናና ቅን ልቦና፣
የስራ ፍቅርና ትጋት፣
ያልተገደበ አስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣
ለለውጥ በጋራ መስራት፤
ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤
ችግር ፈቺነት፤
የማይረካ የመማር ጥማት፤
ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣
ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣