የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በጋራ የጨረራ አመንጪ መሣሪያዎችን ለምርመራና ህክምና አገልግሎት የሚጠቀሙ የጤና ተቋማትን ኢንስፔክሽን አደረገ፡፡ ወራቤ፣ የካቲት/2018 ዓ/ም ኢንስፔክሽኑ የተካሄደው በክልላችን በሰባት መዋቅር የሚገኙ የመደበኛ ራጅ አገልግሎት በሚሰጡ 14 የጤና ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ኤክስሬይ ማሽን በስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በማረጋገጥ ህብረተሰቡ በምርመራ ወቅት ከአላስፈላጊ ጨረራ መጋለጥ ለመከላከልና ደህንነቱን ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። በኢንስፔክሽኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ጉድለት፣ የስራ ፍቃድና እድሳት የሌላቸው፣ የግል ጨረራ ውሰድ መጠን መለኪያ አለመጠቀምና አለማስለካት፣ በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ባልተመዘገበ ባለሙያ ማሰራት ግኝቶች መኖራቸውን በቢሮው የጨረራ ኢንስፔክሽንና የጥራት መሠረተ ልማት ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሙሉዓለም ገዛኸኝ ገልጿል። አቶ ሞገስ ከተማ የክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ተቋማት ፈቃድና ቁጥጥር ኬዝ ቲም አስተባባሪ እንደገለጹት በኢንስፔክሽን ሂደቱ በጥንካሬ የታዩ መቀጠል ያለባቸው መልካም ስራዎች የታዩ ሲሆን በፍጥነት መታረም እና የእርምት እርምጃ በመውሰድ ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን የጤና ተቋማትም መኖራቸውን ከነዚህም ሁለት የግል የጤና ተቋማትን ማሸግ የተቻለ ሲሆን ለስድስት የጤና ተቋማት ከአስር እስከ አስራ አምስት ቀን ውስጥ ጉድለታቸውን እንዲያስተካክሉ በጽሑፍ የቃል ማስጠንቀቂያ በመስጠት ኢንስፔክሽን የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡