Skip to main content
zena93

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር ) በተገኙበት በሰባቱ የክልል ክላስተር ማዕከል ከተሞች 'መሶብ'_ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ግንባታን ማፋጠን በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ምከክር ተካሄደ። የካቲት 23፣ 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር ) በተገኙበት በሰባቱ የክልል ክላስተር ማዕከላት ከተሞች 'መሶብ'_ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ግንባታን ማፋጠን በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል። ርዐሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በመድረኩ ማጠቀሚያ እንደገለፁት ፣ በክልሉ በአሥራ ሰባት ከተሞች 'መሶብ '_የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ነዉ። 'መሶብ'_የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ግንባታዉን በቅድሚያ በሰባቱ የክልል ክላስተር ማዕከል ከተሞች የመጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ ፣ ሥራውን በማፋጠን የአንድ ማዕከል አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ ልዩ ክተትልና ድጋፍ እየተደረገ ነዉ ብለዋል። የዲዛይን፣ የግንባታና መልሶ ግንባታ ሥራዎችን በማፋጠን የቴክኖሎጂ ዝርጋታና የፈርኒቸር አቅርቦት ሥራዎችን በማሳለጥ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱን በአጠረ ጊዜ ለማስጀመር በቅንጅትና በፍጥነት ርብርብ እንዲደረግ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) አቅጣጫ አስቀምጠዋል ። ቀደም ሲል በክልል ደረጃ በሆሳዕና ከተማ በተገነባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከል ዝግጅት ወቅት በተግባር ሂደት የተገኙ ልምዶችን በግብዓትነት መጠቀም እንደሚገባም ጠቁመዋል ። በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተደድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ እና ሌሎች የክልል እና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።