የሰው ሀብት፤ የልማት እቅድ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬቶች
1 የሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የዳይሬክቶሬቱን ሥራ በማቀድ፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም ሥራውን ውጤታማ ማድረግ
• የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣
• ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
• የተቋሙን ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያከናውናል፣
• በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
• በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
• አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
• የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣
2. የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት
- የሴክተሩን ፖሊሲንና ስትራቴጂ መነሻ ያረገ ዕቅድና ሪፖርት ማዘጋጀት
- የበጀት ስረዓትን ማስተዳደር
- በመንግስት በሚመደብ መደበኛና ካፒታል በጀት የሚሰሩ ስራዎች ወይም ተግባራት አፈጻጸምን በማሻሻል የሴክተሩን አቅም ማጎልበት
- የሴክተሩን የዕቅድ አፈጻጸም መከታተልና መገምገም
3. የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
በግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ውስጥ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች
- በየወሩ ስራ ማስኬጃ ገንዘብ፡- ደመወዝ እንዲሁም ካፒታል፣ ወሩ በገባ በ10ኛው ቀን ከፋይናንስ ቢሮ ጠይቆ ማምጣት፤
- ልዩ ልዩ መደበኛ በጀት፣ ካፒታል፣ ዩኒሴፍ፣ ዋን ዋሽ፣ ጂኲፕ እና ሌሎች እንዲህ አይነት ክፍያዎች መመሪያውና ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት መክፈል፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ተቀናሽ ግብርና እንደዚሁም ልዩ ልዩ የአደራ ገንዘብ በመሰብሰብ ወሩ በገባ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው በማስተላለፍ ማስረጃ መውሰድ፤
- ወሩ በገባ በ25ኛው ቀን ለሰራተኞች የሚከፈል ፔይሮል በማዘጋጀት ባንክ በመላክ ከ26ኛው ቀን ጀምሮ አፈጻጸሙን መከታተል፤
- በየወሩ ተሰብሳቢ ሂሳብ በጊዜ መወርዱን መከታተል፤
- የበጀት ዝውውር ስራ መከታተልና መመዝገብ፤
- በየወሩ የሂሳብ ስራዎችን በመከታተል ወሩ በገባ እስከ 10ኛው ቀን የባንክን ሂሳብ መከታተል፤
- በየእለቱ የሂሳብ ምዝገባ በአይቤከስ ሶፍትዌር በመመዝገብ ከቀኑ 10፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ በማስተካከል የማጣራት ስራ መስራት፤
- የዜሮ ሚዛን ሪፖርት ወሩ በገባ በ10ኛው ቀን ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ መላክ፤
- በየወሩ ለኦዲት ስራ መረጃ በማዘጋጀት ሂሳቡ እንዲጣራ በማድረግ ስህተት ቢገኝ አፋጣኝ ማስተካከያ ማድረግ፤
- ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በጀቱን በአግባቡ መክፈልና ስሌቱን ማውረድ፤
- አመታዊ እቅድ በማሰባሰብ የግዢ እቅድ ማዘጋጀትና ከሐምሌ 1-30 ባለው ጊዜ ውስጥ ለግዢ ኤጀንሲ መላክ፤
- የግዢ ፍላጎት መሰረት በማድረግ እስፔስፊኬሽን ማዘጋጀት፤
- የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀትና ጨረታውን በአግባቡ ማጠናቀቅ፤
- የቢሮን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ጥራት ያለው እቃ ገዝቶ ማቅረብ፤
- የዋጋ ጥናት መረጃ ለሚፈልግ ማቅረብ፤
- ለተቋሙ ንብረት መለያ ቁጥር መስጠት፤
- እቃዎችን በመልካቸው ለመለየት ስርአት ባለውና በጥሩ ሁኔታ መዝግቦ መከታተል፤
- በሶስተኛው መጨረሻ አመት የንብረት ቆጠራ ማድረግ፤
- የሚጠገኑና የሚወገዱ እቃዎችን በመለየት በመመሪያው መሰረት ማንሳት፤
- ወደ ሳጥን የሚገባና የሚወጣ ሂሳብ በመከታተል መዝገቡን በመልኩና በጀቱን በርእሱ ለይቶ መመዝገብ፤
- በየእለቱ ሳጥኑን ማስቆጠርና አስፈላጊ ሰነዶችን በደንብ መያዝ፤
- የበጀት አመቱን የሂሳብ ሰነድ በወርና በበጀት ምንጭ ግዢና በሌላ በሌላ የክፍያ ሰነድ ለይቶ በሞዴል 42 መዝግቦ መስጠት ወይም መውሰድ፤
- የግዢ አጠቃላይ ውል ማዘጋጀት፣ ማጽደቅና መረጃ መተንተን፤
- የግዢ መረጃ በመልክ መልኩ በመለየት መመዝገብ፣ የግምገማ ውጤት በቦርድ ላይ መለጠፍና ለህዝቡ ይፋ ማድረግ፤
- ጨረታ የሚከፈትበትን ስነ-ስርአት፣ ንብረት መቁጠርና የተበላሸውን ለይቶ የማስወገድ ስራ የስነ-ስርአት ክፍልና ከውስጥ ኦዲት ጋር በቅንጅት መስራት፤
- የተቆጠረውን ንብረት መመዝገብ፤
- ለለውጥ የታሰበውንና የቡድን ስራ ባህል ማሳደግ፤
- የፈጻሚዎችን አቅም መገንባት፤
- የልምድ ልውውጥ ማድረግ፤
- ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፤