Skip to main content
aply

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር ) በተገኙበት በሰባቱ የክልል ክላስተር ማዕከል ከተሞች 'መሶብ'_ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ግንባታን ማፋጠን በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ምከክር ተካሄደ። የካቲት 23፣ 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር ) በተገኙበት በሰባቱ የክልል ክላስተር ማዕከላት ከተሞች 'መሶብ'_ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት…

በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ያገኘነው እዉቀት ተጨማሪ ገቢ ለማግኝት አስችሎናል ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጠናውን የወሰዱ ዜጎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲኖራቸው ለማስቻል የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠናን በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም በርካታ ወጣቶች አቅማቸውን ለማሳደግ፣ ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ዘመኑን…

በኢትዮጵያ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ እና ወጣቶችን ለወደፊቱ የስራ ገበያ ለማዘጋጀት ታስቦ የተጀመረው የኢትዮ ኮደርስ ፕሮግራም ለሰዎች ዘመኑን የዋጀ እውቀትን እያለበሳቸው ነው፡፡

በግልም ሆነ በተቋም ደረጃ ለሚተገበሩ ስራዎች ውጤታማነት የዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ ነው: ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ። በክልሉ የ 5 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ ተካሂዷል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በዚሁ ጊዜ…

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ 5 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከ157ሺ በላይ ዜጎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማግኘታቸው ተመላከተ። በክልሉ የ 5 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደገለጹት በ5 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከ157ሺ በላይ ዜጎች የብቃት…

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በጋራ የጨረራ አመንጪ መሣሪያዎችን ለምርመራና ህክምና አገልግሎት የሚጠቀሙ የጤና ተቋማትን ኢንስፔክሽን አደረገ፡፡ ወራቤ፣ የካቲት/2018 ዓ/ም ‎ ‎ኢንስፔክሽኑ የተካሄደው በክልላችን በሰባት መዋቅር የሚገኙ የመደበኛ ራጅ አገልግሎት በሚሰጡ 14 የጤና ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ኤክስሬይ ማሽን በስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በማረጋገጥ ህብረተሰቡ…

ተቋማትን በቴክኖሎጂ በማዘመን የተሻለ አገልግሎት መስጠትና ብልሹ አሠራርን በመከላከል የመንግስትን ሀብት ለመጠበቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ። ተቋማትን በቴክኖሎጂ በማዘመን የተሻለ አገልግሎት መስጠትና ብልሹ አሠራርን በመከላከል የመንግስትን ሀብት ለመጠበቅ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስነ-ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና…

የሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሁሉም ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ብቁ እና ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ስርአት እንዲገነባ ልዩ ሚና እንዳለው ተገለጸ። የሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎች በሁሉም ዘርፍ የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን በማገዝ የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ፣ ምርታማነትን በማሳደግ ብቁ እና ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ስርአት እንዲገነባ ልዩ ሚና እንዳላቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን…

ተረጋገጡና ተዓማኒነት ያላቸው ክልላዊ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል የመረጃ ቋት ይፋ ተደረገ።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕላን ልማት ቢሮ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመሆን የለማ የተቀናጀ መረጃ ማሰራጫ ዌብ-ሳይት ርክብክብ ተደርጓል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው በሰጡት ሀሳብ በክልሉ መንግስት የፀደቁና የተረጋገጡ ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎችን ለሁሉም…

በቴክኖሎጂ የታገዘና በዲጂታል ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ብዝሃ ኢኮኖሚ የመገንባት ተልዕኮን ለማሳካት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ድርሻ ጉልህ ነው- የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ (ሆሳዕና፣ ጥር 18/2018)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን የክልሉ ተቋማት የበጀት አመቱን የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አራተኛ ቀን ቀጥሏል። ቋሚ…