በሳይንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራና ስርጸት ዘርፍ
የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃና የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ዳይሬክቶሬት፣
- በሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና የፈጠራ ስራ ለሚያደርጉ ዜጎች ህጋዊ ዕውቅናና ከለላ እንዲያገኙ ማድረግ፤
- የአዕምሯዊ ንብረት መረጃዎችን በማሰባሰብና በመለየት ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት፣
- ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የቅጅ መብት ጥሰት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ተከታታይ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣
- በመንግስት ድጋፍ ከዩኒቨርሲቲዎችና ምርምር ተቋማት የሚወጡ አዳዲስ ግኝቶች ተቋማቱ በባለቤትነት እንዲይዙትና ለተፈለገው ዓላማ እንዲያውሉት ክትትል ማድረግ፣
- ከንግድ ምልክት፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍና ፓተንት ጥበቃ ጋር ተያይዞ ለተገልጋይ የሚሠጡ አገልግሎቶችን ጥራትና ቅልጥፍና መጨመር፣