በሳይንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራና ስርጸት ዘርፍ
የሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት፣
- የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ዉጤታማነትን የሚያሰፍኑ አሰራሮችን መዘርጋት፤
- በሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምርና የፈጠራ ስራ የሚያከናውኑ አካላትን በመመልመል የቁሳቁስ፣ የቴክኒክና፣ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ስራቸው ለተጨባጭ አገልግሎት እንዲበቃ ማድረግ፤
- የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባት በመደበኛ ት/ቤቶች እንዲደራጁና ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን በክልሉ ማህበረሰብ ባህል እንዲሆን በቀጣይነት መስራት፤
- በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዙሪያ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰብና ተቋማትን በመመልመል ማበረታታትና መሸለም፤
- በከተሞች የሳይንስ ካፌዎችንና የቴክኖሎጂ ፓርኮች እንዲቋቋሙ ማድረግ፣
- በመደበኛ ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሳምንታት እንዲከበሩ በማድረግ ሁልአቀፍ መነቃቃት እንዲኖር በማድረግ፣