Admin2
Wed, 12/25/2024 - 10:26

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ቀጥሏል፡፡ ወራቤ፣ ታህሳስ 2017 ዓ/ም በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎችን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ቼክሊስት በማዘጋጀት እና ሁለተኛ የድጋፍ ቡድን በማደራጀት ስምሪት ሰጠ። ==================================
በከምባታ ዞንና በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሳኢቴ መዋቅሮች የድጋፍና ክትትል ስራው ቀጥሏል። የድጋፍ ቡድኑ በዋናነት በየደረጃው የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም፣ በዋና ዘርፎች ታቅደው የተፈጸሙ ተግባራት እና በወል ስራዎች በጥንካሬ የተከናወኑትን በማስቀጠል እንዲሁም በጉድለት የታዩትን በማረም ግብረ-መልስ በየደረጃው የሚሰጥ እንደሚሆን ተገልቷል፡፡