Skip to main content
zena9

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ጀመረ፡፡ ወራቤ፣ ታህሳስ 2017 ዓ/ም በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎችን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ቼክሊስት በማዘጋጀት እና የድጋፍ ቡድን በማደራጀት ስምሪት መሰጠቱን ተጠቆመ። የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በዋናነት በየደረጃው የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም፣ በዋና ዘርፎች ታቅደው የተፈጸሙ ተግባራት እና በወል ስራዎች በጥንካሬ የተከናወኑትን በማስቀጠል እንዲሁም በጉድለት የታዩትን በማረም ግብረ-መልስ በየደረጃው የሚሰጥ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡