Skip to main content
zena8

በክልሉ ትኩረት በተሰጣቸው የልማት ዘርፎች የምርት ጥራትና ምርታማነትን የሚያጎለብቱ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ ስራዎችን በማከናወን ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን አምርቶ መተግበር የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመ:- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት መስራት የሚያስችል መግባቢያ ሰነድ መፈረም መቻላቸው ተሰማ፡፡ በመድረኩ የተገኙት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደገለጹት በሴክተራችን ትኩረት በተሰጣቸው የልማት ዘርፎች እየገጠሙ የሚገኙ ቴክኒካል ችግሮችን በመለየት የሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን በማከናወን ቴክኖሎጂያዊ መፍትሔ ለማፈላለግ በቅንጅት መስራት የጋራ መፍትሔ ለመስጠትና ውስን የሆነውን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ጭምር ዕድል እንደሚሰጥ ገልጸው በተጨማሪም ከምርት ጥራት፣ ምርታማነትና የገበያ ትስስር ጋር በተያያዘ ቴክኖሎጂዎችን የማስፋት፣ የምርምርና ጥናት ስራዎችን በጋራ እንደሚሰሩ አንስተዋል፡፡ እንዲሁም የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በበኩላቸው በተቋማቸው ባለፉት ዓመታት የህብረተሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ በርካታ ቴክኖሎጂዎች በማምረት ወደ ትግበራ የተገባ መሆኑንና ተጨባጭ ውጤቶች መመዝባቸውን አንስተው በተጨማሪም ችግርን ሊፈቱ የሚችሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና ጥናት ለማካሄድ ከክልሉ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚቻል አንሰተዋል፡፡ በመጨረሻም መግባቢያ ሰነዱን በአጭር ጊዜ ወደ ተግባር ለማስገባት የሚያስችል ከሁለቱ ተቋማትና ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ቡድን ማደራጀት ተችሏል፡፡