Skip to main content
zena3

በሀገሪቱ እየተካሔደ ያለውን የእድገት ጉዞ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሳይንስ ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ ወራቤ፣ጥቅምት 22/2017 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊስ እና የኢኖቬሽን አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጥቷል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደገለጹት የሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊስ እና የኢኖቬሽን አስተዳደር ሰርዓት ለመፍጠር ፖሊሲው ወሳኝ ነው ብለዋል። የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ የጠራ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ትኩረት መደረጉን ኃላፊው አብራርተዋል። ሀገር አቀፍ ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ ከየሳይንስ ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን አንጻር በተቋማት ላይ የሚወጡ አገልግሎቶች የሚወጡ ህጎች እና አሰራሮችን መሰረት በማድረግ ለአመራሩ እና ለሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ እየተሰጠ ስለመሆኑም አቶ ሰላሙ ጠቁመዋል። በፖሊሲው የተካተቱ ጉዳዮች እና ትኩረት የተደረገባቸውን ነጥቦች በዝርዝር መመልከት እንደተቻለም ኃላፊው ተናግረዋል። የሳይንስ ፣የቴክኖሎጂ እና የኢኖቬሽን ስራዎች በሁሉም ተቋማት ተግባራዊ በሚሆኑበት ጊዜ በፖሊሲው ቅኝት አንጻር ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ስልጠና እንደነበርም አቶ ሰላሙ አስረድተዋል። በሀገሪቱ እየተካሔደ ያለውን የእድገት ጉዞ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የፈጠራ እና የዲጂታላይዜሽን ስራ አብይ የትኩረት መስክ መሆኑን ጠቁመዋል። ተቋማት ሲስተሞችን እና ድህረ ገጾችን ተጠቅመው ቀልጣፋ እና የዘመነ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸውል ያሉት ኃላፊው ለዚህም የዘርፉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ዝግጁ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት የኢኖቬሽን ኢኮ ሲስተም መዘርጋት የሚያስችል ስርዓት በፖሊሲው መካተቱን ኃላፊው መናገራቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።