
የእምድብር ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት የሳይንስ ሳምንት ማክበሩ አስታወቀ።
ዛሬ በቅዱስ አንጦንዮስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ በተከበረው የሳይንስ ሳምንት የተለያዩ መርሃ-ግብሮች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህም መሃከል ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎች ገለፃ፣ተሞክሮዎች እና የጥያቄና መልስ ውድድር የተካሄደ መሆኑን የፅ/ቤቱ ኀላፊ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ኬርጋ ገልፀዋል።
ለሳይንስ ሳምንት ታዳሚው የተለያዩ የፈጠራዎች ባለቤት የሆነው እና በሃገር አቀፍ ደረጃ ስራዎቹን እያቀረበ እውቅና ያተረፈው ተማሪ አቤል ፍቃዱና ኢንጂነር መልካሙ መለሰ ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎች ገለፃ፣ተሞክሮዎች አቅርበዋል።
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የእምድብር ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ ኢንጂነር አብድላዚዝ ከማል ከራሳቸው የህይወት ተሞክሮ ባሻገር ለተማሪዎቹ ምክር የለገሱ ሲሆን ለተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ባለቤት ለሆነው ለተማሪ አቤል ፍቃዱ አድናቆታቸውን በመቸር እንደ ከተማ አስተዳደር ከአቤል ጋር በመናበብ ወደ ፊት የጋራ የምናረጋቸው ተግባራት ይኖራሉ ሲሉ ተደምጧል።
የእምድብር ከተማ አስተዳደር ት/ፅ/ቤት ኀላፊ የሆኑት አቶ አለሙ በርክትም ያለ ት/ት ቴክኖሎጂ ብዙ ርቀት መጓዝ አይችልምና ከቴክኖሎጂ ጋር መግባባት ይኖርብናል ሲሉ ተደምጧል።
በእምድብር ከተማ የሚገኙ እነ አቤኔዘር መርጃን፣መልካሙ መለሰ እና አቤል ፍቃዱ የፈጠራ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች መላ የተሰኘ የአፕሊኬሽን እና የሶፍት ዌር ፈጠራ ስራ ግሩፕ መስርተው እየሰሩ ስለሚገኙ ፍላጎት ያለው የትኛውንም ግለሰብ መቀላቀል ይችላል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ከእምድብር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከቅዱስ አንጦንዮስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በተገኙ ተማሪዎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ የተመለከቱ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄዶ ከቅዱስ አንጦንዮስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ አቤል ፍቃዱ 1ኛ በመውጣት ከእምድብር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተገኘው ተማሪ ፍሬሁን ክብሩ 2ኛ በመውጣት የተሸለሙ ሲሆን በጠቅላላ የፈጠራ ስራ ደግሞ ተማሪ አቤል ፍቃዱ ልዩ ተሸላሚ ሆኖ የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆኗል።