
ቢሮው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራና ስርፀት ዘርፍ ስራዎች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቡታጅራ ከተማ ማዕከል ለዞንና ልዩ ወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰላሙ አማዶ ስልጠናው ያስጀመሩ ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ተወዳዳሪነት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የፈጠራ ስራዎች ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ዘርፉን በተገቢው መደገፍ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በፈጠራና የሳይንስ ስራዎች ያልታገዘ እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜና ገንዘብ ለውጥ ማምጣት አይቻልም የሚኖረውም ለውጥ አዝጋሚ መሆኑ በዘርፍ ተጠቃሚ ከሆኑ አካባቢዎችና ሃገራት ተወዳዳሪ ለመሆን ዘርፍን በተገቢው መጠቀም እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በክልሉ በፈጠራ ስራዎች በተለያዪ አካባቢዎች እስከሃገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ተቋማት መታቀፍ የቻሉ አበረታች የፈጠራ ስራዎች መኖራቸው ገልፀው ከትምህርት ቤቶችና ተቋማት ደረጃ ተመሳሳይ የሆኑ ፈጠራ ስራዎች ለማውጣትና ለማበረታታት ስራዎች እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ስልጠና ለአመራርና ባለሙያዎቹ ከዞን እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ያሉ የፈጠራ ስራዎች ፋይዳቸውን በመረዳት የትኞቹን ስራዎች ቅድሚያ መስጠትና እንዴት መለየት እንደሚችሉ የልየታ መስፈርቶች በመያዝ አስፈላጊ የሆነው ድጋፍ ለማድረግ እንደሚረዳቸው ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም የፈጠራ ስራዎች ሞዴል ምርት የማምረት ደረጃ በማድረስ ያስፈልጋል አልፎም ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች፣ ከኢንዱስትሪ ተቋማትና ሌሎች ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት ህብረተሰብ ተጠቃሚ እንዲሆንባቸው ማሰራጨትና ማስፋት የሚችሉበት አግባብ ግንዛቤ የሚፈጥር ስልጠና መሆኑ አመላክተዋል።
ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል ።