Admin2
Mon, 08/17/2026 - 14:44
የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርስቲ ጋር በቅንጅት ልዩ ተስጥዖ ላላቸው የፈጠራ ባለቤቶች የክረምት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተሠማ
ወራቤ ነሐሴ/2028 ዓ/ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርስቲ በጋራ ልዩ ተስጥዖ ላላቸው የፈጠራ ባለቤቶች በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ; በሳይበር ደህንነት፣ ሮቦቲክስ፣ የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ፣ አይሮዳይናሚክስ፣ በድሮን ቴክኖሎጂ፣ በኬሚካል ምህንድስና የክረምት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የቢሮው ምክትል እና የሳይ/ቴክ/ፈጠራና ስርፀት ዘርፍ ኋሌፊ የሆኑት አቶ ሙሂዲን ሁሴን ዩንቨርስቲው ከመላው የሀገሪቷ ክፍል በተለያዩ የጦር መሣሪያዎች የፈጠራ ስራ ልዩ ተስጦዖ ያላቸውን የፈጠራ ባለቤቶች/ተማሪዎች ለተከታታይ 30 ቀናት ዩንቨርስቲ በማስገባት የተሟላ ሎጀስቲክ በማሟላት ስልጠናውን ከክልላችን ልዩ ተስጥዖ ያላቸው ፈጠራ ባለቤቾች እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ስልጠናው ከንድፈ ሀሳብ ወደ ተግባር የሚያስገባ ሲሆን ከ2017 ዓ/ም የቀጠለ ስልጠና እንደሆነ ተገልጿል።