Admin2
Thu, 08/13/2026 - 14:37
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለክልሉ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አገልግሎት የሚያዘምን ሲስተም እንደሚለማ ተሠማ
ወራቤ ነሐሴ/2028 ዓ/ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የክልሉን ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን የሚያስችል አዲስ የዲጂታል ሲስተም ሊያለማ መሆኑ ተገለጸ።
ሲስተሙ ከልደት፣ ከጋብቻ፣ ከፍቺ እና ከሞት ምዝገባ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ለማድረግ ያለመ ነው።
አሰራሩን ወደ ዲጂታል ማሸጋገር የህብረተሰቡን እንግልት ከማስቀረቱ ባሻገር የመረጃ ጥራትንና ደህንነትን አስተማማኝ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
የቢሮው እንቅስቃሴ በክልሉ የመንግስት አገልግሎቶችን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመደገፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ለማሳካት ከተያዙ እቅዶች አንዱ አካል መሆኑ ተመላክቷል።
በመድረኩ የተቋማቱ ኋላፊዎች; ሲስተም አልሚዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።