Admin2
Wed, 05/20/2026 - 00:52
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባብያ ስምምነት ተፈራረመ። በስምምነቱ ወቅት ዲጂታላይዜሽን እና ቱሪዝም ዘመኑ የደረሰበት እና ዓለም እየተራመደ ባለበት ዘመን በተመጣጠነ እና በሚፈለግበት ደረጃ ለመራመድ በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑ ተመላክቷል።
ሀገር የምትፈልገው እና ክባቢው ካለበት እውነት ጋር በማጣጣም ለመስራት ዓላማውን ያደረገ ስምምነት መሆኑ ከቀረበው ንድፈ ሃሳብ መረዳት ተችሏል። ጥናቱ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚካሄድ ሲሆን ሲጠናቀቅ ቱሪዝምን ጨምሮ የክልሉን ጸጋዎች ጂአይ ኤስ ጋር በማስተሳሰር የቱሪዝም ሴክተር ለማጉላት የሚያግዝ መሆኑ ይጠበቃል።
የመግባቢያ ስምምነቱን ዩኒቨርሲቲያችን አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት እና የፕሬዚደንት ተወካይ ዶክተር ሃብቴ ዱላ እና የክልሉ ሳይንስ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የሳይንስ ፈጠራ እና ስርጸት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን ተፈራርመዋል። ስራው በዩኒቨርሲቲው እና በክልሉ መካከል በጋራ የሚሰራ መሆኑን የውል ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ተገልጿል። ጥናቱ ተጠናቆ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚገባም ጥቆማ ተሰጥቷል።