Skip to main content
zena102

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል አስፈላጊ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ (ሆሳዕና፦ ሚያዚያ 30/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለዘርፉ ባለሙያዎች በሶፍትዌር ማበልፀግ ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደገለፁት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በዘረፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል አስፈላጊ ነው ብለዋል። በክልሉ ከዲጂታል ቴክኖሎጂው ጋር የተላመደ ማህበረሰብ ለመፍጠር ቀደም ሲልም በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት በተለያዩ ዙሮች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ስለመሰጠቱ ገልፀዋል።

በመንግስት ደረጃ የታቀደውን ዲጂታል አሰራሮችን ለማስፋፋትና የታቀደውን ዕቅድ እውን ለማድርግ በክልሉም በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለው ይህን አሰራሮችን ማላቅ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉበት እንደሆነም ገልፀዋል ለተገልጋዩ የሚሰጠው የትኛውም አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ መታገዝ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሰላሙ ይህ ደግሞ አሰራሮችን በማቀላጠፍ እንግልት እና ብልሹ አሰራሮችን የሚያስቀር ነው ብለዋል። አሁን እየተሰጠ ያለው ስልጠና ሶፍትዌሮችን ማበልፀግ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞችም ከክልሉ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ስለመሆናቸውም ጠቁመዋል። ስልጠናው ተግባር ተኮር መሆኑን የገለጹት ኃላፊው በዘርፉ የሚታየውን የእውቀት ክፍተት እንደሚሞላ ጠቁመዋል።