Skip to main content
zena100

የዲጅታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም መገንባት ወሳኝ ነው፡- አቶ እስጢፋኖስ ጡራሞ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለዞንና ለልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የኢኮቴ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ለአራት ተከታታይ ቀናት በወራቤ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ወራቤ፣ ሚያዚያ 17/2018ዓም፡- የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሶፍት ዌር ልማት፣ በኔትወርክ መሰረተ ልማት እንዲሁም በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከዞንና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ለአይሲቲ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የኢኮቴ ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ተወካይ አቶ እስጢፋኖስ ጡራሞ እንዳሉት ዓለም ወደ አንድ መንደር እየመጣ ባለበት በዚህ ዘመን ከቴክኖሎጂ ውጪ መሆን አይቻልም፡፡ በዚሁ መነሻ የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከተጣለበት ኃላፊነት በመነሳት ክልሉን የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም በአዳዲስ የቴክኖሎጂ በመገንባትና በማብቃት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ በተለይ የዲጂታል ኢትዮጵያ ትልም 2030 እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቢሮው የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ አቶ እስጢፋኖስ አክለውም በቀጣይም ይህን መሰለን ተከታታይነት ያለው ስልጠና በመስጠት ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት አስረድተዋል፡፡ ሰልጣኞች በአራት ቀን የወሰዱትን ስልጠና በየተቋማቸው ወደ ተግባር መቀየር ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም የእውቀት ሽግግር ማድረግ አለባቸው ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች ገንቢ የሚሏቸውን ሀሳብ አስታያየቶች ሰንዝረዋል ይህን መሰል የክህሎት ስልጠና መሰጠቱት የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት፣ እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዘርፉ ትርጉም ያለው ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ፋይዳው የጎላ ነው መሰረት ይጥላል ብለዋል፡፡