Admin2
Thu, 04/16/2026 - 18:15
በባለፉት 9 ወራት በመሳሪያዎች ቴክኒካል ግምገማ፣ የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገናና ዕድሳት አገልግሎት በመስጠት ከመንግስት ይወጣ የነበረው 10 ሚሊዮን 531 ሺህ 852 ብር ማዳን መቻሉን የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ገለጸ።
ሚያዝያ 6/2018ዓ.ም(ወልቂጤ) የጉራጌ መስተዳድር ምክር ቤት የባለፉት 9ወራት እቅድ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ እየገመገመ ነው። የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንዳሉት በዞኑ በባለፉት 9 ወራት የካይዘን ትግበራ በትኩረት በመሰራቱ የጊዜ ብክነት መቀነስ፣ የገንዘብና የስራ ጥራት ማረጋገጥ ተችሏል። ኢትዮ ኮደርስ 42 ሺህ 690 ዜጎች የሰለጠኑ መሆኑን አንስተው በዚህም 40 ሺህ 571 ዜጎች ሰርተፍኬት ማግኘታቸውን አንስተዋል። በመሳሪያዎች ቴክኒካል ግምገማ፣ የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገናና ዕድሳት አገልግሎት በመስጠትና በዙም ሚቲንግ ከመንግስት ይወጣ የነበረው 10 ሚሊዮን 531 ሺህ 852 ብር ማዳን መቻሉን አንስተዋል።
በባለፉት ዘጠኝ ወራት ለመንግስት ተቋማት 8 ሲስተሞችን ማልማት መቻሉን ጠቁመው ከዚህም ባሻገር 7 ዌብሳይት ማልማት መቻሉንም ተናግረዋል።