በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ስራ ለሚጀምረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዘርፉ የተመደቡ ባለሙያዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም ጋር የልምድ ልውውጥ አደረጉ ።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባብያ ስምምነት ተፈራረመ። በስምምነቱ ወቅት ዲጂታላይዜሽን እና ቱሪዝም ዘመኑ የደረሰበት እና ዓለም እየተራመደ ባለበት ዘመን በተመጣጠነ እና በሚፈለግበት ደረጃ ለመራመድ በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑ ተመላክቷል።
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል አስፈላጊ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ (ሆሳዕና፦ ሚያዚያ 30/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለዘርፉ ባለሙያዎች በሶፍትዌር ማበልፀግ ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው።
ክልሉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ የባለሞያዎች ቴክኒካል ክህሎት ማሳደግ ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ። (ወራቤ፣ ሚያዝያ 21 /2018)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ባለሞያዎች በሆሳዕና ከተማ ሲሰጥ የቆየው 2ኛ ዙር ቴክኒካል ስልጠና ተጠናቀቀ።
የዲጅታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም መገንባት ወሳኝ ነው፡- አቶ እስጢፋኖስ ጡራሞ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለዞንና ለልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የኢኮቴ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ለአራት ተከታታይ ቀናት በወራቤ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ወራቤ፣ ሚያዚያ 17/2018ዓም፡- የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለአራት…
የሀገር በቀል እውቀቶችን ከሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ጋር በማቀናጀት ኢኮኖሚውን ለማጠናከር በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገለጸ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) መር ዘላቂና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ጋር ማቀናጀትና ማዘመን ላይ ያተኮረ ለዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
የክልሉን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሞያዎች አቅም በዲጅታል ቴክኖሎጂ ክህሎት በማሳደግ የዜጎች አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እየተሰራ ነው:-የክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ (ሆሳዕና፣ ሚያዝያ) 14/2018)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሶፍትዌሮችን ማበልፀግ የሚያስችል ስልጠና ለዘርፉ ባለሞያዎች እየሰጠ ይገኛል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ…
በባለፉት 9 ወራት በመሳሪያዎች ቴክኒካል ግምገማ፣ የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገናና ዕድሳት አገልግሎት በመስጠት ከመንግስት ይወጣ የነበረው 10 ሚሊዮን 531 ሺህ 852 ብር ማዳን መቻሉን የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ገለጸ።
ሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ የጋራ ትብብር በማድረግ ዘመናዊ የድረ-ገጽ ልማት አጠናቀው በይፋ ስራ አስጀመረ። ይህም የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን ለተገልጋዮች ከአንድ ቋት የተለያዩ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ጤና ተቋማት የሚጠቀሙትን የጨረራ አመንጪ መሳሪያዎች ብቃትና ደህንነት በየግዜው በማስፈተሽና ህግና አሰራር ተከትለው በመስራት የማህበረሰቡን ጤና ደህንነት መጠበቅ እንዳለባቸው ተገለጸ። መጋቢት 4/2018 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤናና ጤናነክ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በጤና ተቋማት የጨረራ አመንጪ የሆኑ የህክምና መሳሪያዎች ላይ…