ሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ የጋራ ትብብር በማድረግ ዘመናዊ የድረ-ገጽ ልማት አጠናቀው በይፋ ስራ አስጀመረ። ይህም የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን ለተገልጋዮች ከአንድ ቋት የተለያዩ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል።
የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ በስራው ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ እንዳሉት ዲጅታል ቴክኖሎጂ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ለተገልጋዮች ቀልጣፋና ቀላል አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ሚና አለው። ቢሮውም በትምህርት ሴክተር የዲጅታል ቴክኖሎጂን ዕውን ለማድረግ በትኩረትና በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አቶ ከበደ ሻሜቦ በአጽንኦት ተናግረዋል።
ዘመኑ የቴክኖሎጂ እንደመሆኑ በክልሉ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው በቴክኖሎጂ የታገዘ እንሆን የማስቻል ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ ገልጸዋል። ቢሮው ለሆሳዕና ትምህርት ኮሌጅ አልምቶ ወደ ስራ ያስገበው ድረ-ገጽ የዚህ አካል መሆኑን የጠቀሱት አቶ ከበደ ይህም የትምህርት ስርዓትን ውጤታማ ለማድረግ ጉልህ ሚና እንዳለው አብራርተዋል። በተለይም የተለያዩ አጋዥ መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት ማሳተም ሳይጠበቅ ተደራሽ ለማድረግ ብሎም ልዩ ልዩ ትምህርታዊ ስልጠናዎችን መምህራንና ተማሪዎች በቀላሉ ከድረ-ገጹ ማግኘት እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አቶ ከበደ ሻሜቦ አብራርተዋል።
ዘመኑን የሚመጥን መረጃ ፍሰትን የሚያቀላጥፍ ድረ-ገጽ እንደሚያስፈልግ በሙሉ ተነሳሽነትና በቅርበት ስራውንም ስከታተልና ስያሰራ የቆየው የኮሌጁ አካዳሚክ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን ዶ/ር ደስታ በቀለ በይፋዊ ስራ ማስጀመሪያ ዕለት ተገኝተው ይህ ስራ ትኩረት የሚያስፈልግ የዘመኑ ዲጂታል ቴክኖሎጂ መተግበሪያ መሣሪያ እንደሆና በአጽንኦት ተናግሯል።
የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አባይነህ ኤርጎጎ በድረ-ገጽ ስረ ማስጀመሪያ እንደገለጹት ይህም ጊዜና ወጪን በማዳን የኮሌጁን አገልግሎት በአንድ ቋት ለብዙሃኑ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸው የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮና የኮሌጁ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት በጋራ ለሰሩት ስራ እና ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።