Skip to main content
aply

ተቋማት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በብቃት እንዲጠቀሙ የሚያስችል አቅም ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለጸ። ቢሮዉ ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ ባለሙያዎች በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ጥገናና እድሳት ላይ ያዘጋጀው የተግባር አቅም ግንባታ ስልጠና በወራቤ ከተማ እየተሰጠ ነዉ። ስልጠናውን ያስጀመሩት የቢሮው ምክትልና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና…

ህዳር 6/2017 ዓ.ም በሳይንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ከኢንተርፕሪነር ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት ለዞን፣ ለልዩ ወረዳ አመራሮችና ለባለድርሻ አካላት ለተከታታይ 3 ቀናት በወልቂጤ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን…

ህዳር 4/2017 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢንተርፕሪነር ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት ለዞንና ለልዩ ወረዳ አመራሮችና ለባለድርሻ አካላት ስልጠና በወልቂጤ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል። ስልጠናው በፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕ እና ኢኖቬሽን ኢኮሲስተምና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ አሰጣጥና አስተዳደር ዙሪያ ለ3 ተከታታይ ቀናት በመስጠት ላይ ነው። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ…

ኢትዮ ኮደርስ በክልሉ በሥራ ዕድል ፈጠራ የሚኖረው አበርክቶ ጉልህ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ ተናገሩ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የሀገሪቱን ዲጂታል ክህሎት ከፍ ለማድረግ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ዲጂታል ኮደርስ የሚኖረው አበርክቶ ጉልህ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ አንተነህ ይህን የተናገሩት የዋን- ዋሽ፣ የኮ-ዋሽ ፕሮግራም…

በሀገሪቱ እየተካሔደ ያለውን የእድገት ጉዞ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሳይንስ ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ ወራቤ፣ጥቅምት 22/2017 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊስ እና የኢኖቬሽን አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጥቷል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደገለጹት የሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊስ እና የኢኖቬሽን አስተዳደር…

ዘመኑን የዋጀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና ያላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች አቅም መገንባት ወሳኝ ነው፡- አቶ ከበደ ሻሜቦ ዘመኑን የዋጀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና ያላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትልና የኢኮቴ ልማት እና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ ገለፁ። ቢሮው በክልል ሴክተር መ/ቤቶች፣ በዞን እና በልዩ ወረዳ መዋቅሮች፣ በወራቤ…

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በተመለከተ ባስተላለፉት መልእክት ለዲጂታል ኢትዮጵያ መሳካት የሰለጠነ የሰው ሃይል ማዘጋጀትና ወደ ስራ ማስገበታ ወሳኝ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይህንን ለማገዝ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮጀክት ተግባራዊ በማድረግ በሁሉም ክልሎች ያሉ ወጣቶች የመንግስት ሰራተኞች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ክህሎት የማልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል::