
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ ( ዶ/ር) ፣የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሮጀክቶች አስተባባሪ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ብርሀኑ ተስፋዬ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዛሬው እለት ተመርቆ ስራ የጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 5 የፌደራል እና 2 የክልል ተቋማት 20 አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን ስራ ጀምረዋል። በማዕከሉ ንግድና ገበያ ልማት፣ገቢዎች፣ኢሚግሬሽን፣ንግድ ባንክ፣ፖስታ አገልግሎት ፣ፋይዳ እና ኢትዮ ቴሌኮም በነዚህ ተቋማት 20 አገልግሎት መስጠት ያስችላል ተብሏል። ተቋሙ ወደፊት ከ60 በላይ አገልግሎት ማስተናገድ የሚችል ስለመሆኑም ተመላክቷል። በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ ዲጂታላይዝድ ፣የተገልጋዩን ህብረተሰብ ጊዜ ወጪ ፣ሀብት እና እንግልት የሚቀንስ ሲሆን የአገልግሎት ጥራት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሻሽል ስለመሆኑም ተመላክቷል።