በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከባለሙያዎችና ከሠራተኞች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ።ታህሳስ 27/2018 ዓ/ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ፤ ችግር ፈቺ የምርምርና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶችን በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለጸ። ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማውን ከተቋሙ መላው ሠራተኞች በጋራ በሆሳዕና ከተማ ግምገማ አካሂዷል። የቢሮው ምክትል ኃላፊና የሳይንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራና ስርፀት ዘርፍ ኋላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ቢሮው ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት በቴክኖሎጂ የበለጸገ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል። አክለውም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በተለይም ውጤታማና ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ለማሳደግ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩንቨርሲቲዎች) እና ከተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የተሻለ; አበረታች ውጤቶች የተመዘገበበት በሂደቱም የተስተዋሉ ውስንነቶችን በመገምገም በቀጣይ ማረም እንደሚገባ ተነስቷል። ቢሮው በ6ወራት ቅንጅታዊ አሰራሮቾን በማጠናከር በተለይ ከሚ/ር መ/ቤት; ከተጠሪ ተቋማት; ከዩንቨርስቲዎችና ከተቋማት በጋራ በዲጂታላይዜሽን; በኢኖቬሽን እና በምርምርና ጥናት ስራዎች ትግበራ በጋራ እየተሠራ ይገኛል። የቢሮው ምክትልና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ በበኩላቸው፤ መንግስት የዘረጋውን ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ስትራቴጂ ስኬታማ ለማድረግ የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። ተቋማዊ አሠራሮች ተቀናጅተው መሄዳቸው ለጥናትና ምርምር ሥራዎች ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ገልጸው በግማሽ ዓመት በርካታ የተከናወኑ ተግባራት የመንግስት ተቋማትን ለማዘመን የሚያስችሉ እንዲሁም የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎች የተሰራበት እንደሆነ አክለው አንስተዋል። የቢሮው ኃላፊ አማካሪ የሆኑት አቶ ሁሴን ሳኒ ተቋሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባስመዘገበው የተሻለ አፈጻጸም እውቅና ባገኘበት ወቅት የተካሄደ መድረክ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠልና የታዩ ጉድለቶችን በማረም ረገድ የሁሉንም አካላት ቁርጠኝነት ጠይቀዋል። በዕለቱ የቢሮው የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮ ልማት ዕቅድና በጀ/ዝግ/ክት/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ፀጋዬ ወንድሙ በዝርዝር ቀርቧል። በመድረኩ የተገኙ የቢሮ ባለሙያዎችና ሠራተኞች ሪፖርቱን በዝርዝር ገምግመው በጥንካሬ የተሰሩ ተግባራትን በማሰቀጠል በጉድለት የታዩ በቀጣይ ጊዜ በማረም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም መረባረብ እንደሚገባና ሚናቸውን እንደሚወጡ አንስተዋል።