Skip to main content
zena81

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ1ኛ ግማሽ ዓመት ስራዎች ክትትልና ድጋፍ ስራ ማድረግ ጀመረ። ‎ወራቤ: ታህሳስ/2018 ዓ/ም ‎ ‎የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በዞንና በልዩ ወረዳ ሳኢቴ መዋቅሮች የ2018_በጀት_ዓመት የ1ኛ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ ቡድን በማሰማራት እየገመገመ ይገኛል። ‎‎በክትትልና ድጋፍ ስራ የታዩ ዋና ዋና ተግባራት:- ‎የሪፎርም ትግበራና እና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም አተገባበር; በየመዋቅሩና ተቋማት የዲጂታላይዜሽን ትግበራ እና የኢኖቬሽን/ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ ስራዎች; ‎እንዲሁም ሌሎችንም ተግባራት በማካተት በጥንካሬ የተፈፀሙትን አጠናክሮ በማስቀጠል በሂደቱ መሻሻል የሚገባቸውን ተግባራት በመገምገም የሚያርም ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።