ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት በክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ቢሮ የለማዉን ዌብሳይት ተረከበ ። ምክር ቤቱ በክልሉ ህገመንግስት የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት እንዲሁም ተቋሙ የምያከናዉናቸዉን ተግባራት መረጃ ለማሰራጨት ዌብሳይቱ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የምክርቤቱ ዋና አፈጉባኤ ክቡር አቶ አቡቶ አኒቶ የገለፀው ሲሆን ይህን ዌብሳይት በጥንቃቄ በመስራት ላስረከበዉ የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በራሳቸውና በምክር ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል ። የቢሮዉ ሶፍትዌር ዴቨሎፐር ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙከረም ሳኖ በበኩላቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች አጠቃቀምንና አቅርቦት ከማሳደግ አንጻር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 38 ዌብ ሳይቶችን እና 19 ስስተሞችን ማልማትና15 ስስተሞች ከስተማይዝ ማድረግ መቻሉ ገልፀው በዘንድሮው በጀት ከዚህ ከዚህ በበለጠ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል ። ቢሮው አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ በማድረግ ብልሹ አሰራርን በመቀነስ ብሎም በማስቀረት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ መጠነ ሰፊ ስራዎች እየሰራ ነው ብለዋል። የዚህም አካል የሆነው የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዌብሳይት ዛሬ መጠናቀቅ መቻሉን ገልፀው በቀጣይ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አጠቃላይ ማኑዋል ሲስተሙን ዲጂታል በማድረግ ሂደት ውስጥ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የበኩሉን እንደሚወጣ ተናግሯል ።