Skip to main content
zena79

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን እንዲሁም ከክልሉ ጤና ቢሮ በጋር በቅንጅት የጨረራ አመንጪ መሣሪያዎችን ለምርመራና ህክምና አገልግሎት የሚጠቀሙ የጤና ተቋማትን ኢንስፔክሽን አደረገ፡፡ ወራቤ፣ ታህሳስ/2018 ዓ/ም ኢንስፔክሽኑ የተካሄደው በክልላችን በሚገኙ ዞኖች ካሉ የጤና ተቋማት ውስጥ ዘጠኙ/9/ ላይ ህክምና መመርመሪያ መሳሪዎች ኤክስሬይ ማሽን፣ ሲቲስካን ማሽን፣ ፍሎሮስኮፒና ማሞግራፊ ማሽኖች ከሚመነጭ ጨረር ህብረተሰቡን ለመከላከልና ደህንነቱን ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። በኢንስፔክሽኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ የሙያ ፍቃድ፣ የስራ ፍቃድና እድሳት፣ የግል ጨረራ ውሰድ መጠን መለኪያ አለመጠቀምና አለማስለካት፣ በኢት/ያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ባልተመዘገበ ባለሙያ ማሰራት፣ scattered radiation /ያልተፈለገ ጨረራ በ waiting area/ወደ ህብረተሰቡ ከስታንዳርድ በላይ አፈትልኮ እንደሚወጣ ግኝቶች መኖራቸውን በቢሮው የጨረራ ማሳወቅና ፍቃድ አሰጣጥ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሙሉዓለም ገዘሐኝ ገልጿል። አቶ ወንድማገኝ አድማሱ በባለስልጣን መ/ቤት የጨረራና ኑውክላር ቴክኖሎጂ ሲፍቲ ኢንስፔክሽን ከፍተኛ እክስፐርት እንደገለጹት በኢንስፔክሽን ሂደቱ በጥንካሬ የታዩ መቀጠል ያለባቸው መልካም ስራዎች የታዩ ሲሆን በፍጥነት መታረም እና የእርምት እርምጃ በመውሰድ ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን የጤና ተቋማትም መኖራቸውን አውስተው /ከአምስት እስከ አስራ አምስት ቀን ውስጥ እንዲያስተካክሉ በጽሑፍ የቃል ማስጠንቀቂያ በመስጠት የመጀመሪያ ዙር ኢንስፔክሽን የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡