በ2025 ዓ.ም ዲጂታል ኢትዮጲያን ዕዉን ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ። የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በወረዳኔት መሳሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ለዞን ፣ለልዩ ወረዳና ለከተማ አስተዳደር ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር እየተሰጠ ይገኛል። ሕዳር 4/2018 ስልጠናዉን በንግግር ያስጀመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የሰዉ ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክተር አቶ በቀለ አራርሳ ባስተላለፉት መልዕክት በ2025 ዲጅታላይዜሽን እዉን ለማድረግ የአቅም ግንምባታ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸዉን ተናግረዋል። ከአቅም ግንባታ ማጎልበቻ ስልጠናዎች አንዱ የሆነዉ የወረዳኔት መሳሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም ላይ የተኮረ ስልጠና ለዞን ለልዩ ወረዳና ለከተማ አስተዳደር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታና የአሰልጣኞች ስልጠና በክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አዘጋጂነት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። ሰልጣኞቹ ስልጠናዉን በተገቢዉ በመከታተል ዲጅታል ኢትዮጲያን እዉን ለማድረግ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ማበርከት አለባቸዉ ብለዋል። ስልጠናዉ ከህዳር 04/2018 እስከ ህዳር 06/2018ዓ ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥል አቶ በቀለ ጠቅሰዋል። በወረዳኔት አያያዝና አጠቃቀም (በADSL) አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በቢሮዉ የመንግስትና የማህበረሰብ መረጃ አስተዳደር ዳይሬክተር በአቶ ኢስጥፋኖስ ጡራሞ እየተሰጠ ይገኛል። በስልጠናዉ በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ በቀለ አራርሳ፣ በቢሮዉ የመንግስትና የህዝብ መረጃ አስተዳደር ዳይሬክተር እና የስልጠናዉ አሰልጣኝ አቶ ኢስትፋኖስ ጡራሞን ጨምሮ ፣ከዞን፣ ከልዩ ወረዳእና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ ሰልጣኝ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።