Admin2
Fri, 07/18/2025 - 21:49

የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሴክተር ጉባዔ ለባለድርሻ አካላት ዕውቅና በመስጠት አበረታታ፡፡ በመድረኩ ቢሯችን ከተቋማት ጋር በፈጠረው ቅንጅታዊ አሰራር የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘምን በማድረግ ረገድ ለክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የነዳጅ መቆጣጠሪያ ሲስተም ልማት፣ ዌብሳይት ልማት እና የንግድ ፍቃድና ዕድሳት ስራ ላን ማስፋት እና የፋብሪካ ምርቶች ላይ የምርት ጥራት ኢንስፔክሽን ስራዎች ከተቋሙ በጋራ በመስራታችን ለተገኘው ውጤትና ለተሰጠው ዕውቅና የቢሮው ኃላፊ አቶ ሠላሙ አማዶ ልባዊ ምስጋና እያቀረቡ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡