Skip to main content
zena56

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አገልግሎት በማዘመን የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየሰራ ያለው ተግባር አበረታች መሆኑን ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ።  ሀምሌ 10/2017) የምክር ቤቱ የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል። የምክር ቤቱ የማህበራዊ ጉዳዮች የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ ቢሮው እየሰራ ያለው ተግባር አበረታች ነው ብለዋል። በዲጂታላይዜሽን እና በፈጠራ ስራ ድጋፍ የተሰሩ ስራዎች አበረታች እና የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ በመሆኑ ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት። የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተሰራ ያለው አበረታችና ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች በቀላሉ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ሲስተም; ዌብሳይት ልማት; ከስተማይዜሽን እና የፈጠራ ስራዎችን ደግፎ ወደ ልማት የማስገባት ስራዎችን አበረታች መሆኑን ተናግረዋል። ከቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ ጥያቄዎች የቢሮ ኃላፊና ማኔጅመንት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።