Skip to main content
zena38

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኋላፊ አቶ ሠላሙ አማዶ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ በዓሉ አንድነትን ይቅርታን ታናሽነትን መተሳሰብን ለወንድም እና እህትን በማገዝ የሚገለጽበት በመሆኑ በተለይ በህመም ላይ ያሉ ፣ ወላጆቻቸውን በተለያየ አጋጣሚ በህይወት ከጎናቸው የሌሉ፣ አቅመ ደካማ ወገኖቻችንን በመጠየቅ ፣ በመረዳዳት በማካፈል አብሮ በዓሉን ማክበር ይገባል ብለዋል በመጨረሻም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች በሙሉ በድጋሚ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡