
ቢሮው ዲጂታል ቴክኖሎጂ በመጠቀም የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ሳሙኤል ዳርጌ ገለጹ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር የመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች ለመመዝገብ እና ለመቆጣጠር በለማ ሶፍት ዌር ግብዓት ለማሰባሰብ ውይይት ተካሂዷል ፡፡ በስጦታ አሊያም በግዢ የገቡ ንብረቶችን መመዝገብ ፣በባለሙያ ተፈትሾ ማሳለፍ ፣ የንብረቱን ደህንነቱን መቆጣጠር ፣ ስርጭት እና ቁጥጥር መስራት ፣ተመዝግቦ በመጋዘን የሚገኙ ንብቶችን ብዛት እና ያሉበትን ደረጃ የመቆጣጠር ስራዎችን መስራት የሚችል ሶፍት ዌር መሆኑ ተገልጿል ፡፡ ሶፍት ዌሩ የክልሉ ጤና ቢሮ ለተቋማት እና ህክምና መስጫ ማዕከላት የሚያደርገውን የመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች ስርጭት ምዝገባ እና ቁጥጥር መስራት የሚችል መሆኑ የሶፍት ዌሩ አዘጋጆች ገልጸዋል ፡፡ የሁለቱ ቢሮ ኃላፊዎች እና ማኔጅመንት በተገኙበት በለማው ሶፍት ዌር አጠቃላይ ገጽታ ላይ በባለሙያዎች ገለጻ እና ማብራሪያ ቀርቧል ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ እንዲሰራ ከታሰበው በተሻለ የቢሮው ባለሙያዎች ማልማታቸውን ገልጸው ለክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ እና ለአዘጋጆቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡ የጤና ቢሮ አገልግሎትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን ገልጸው ሶፍት ዌሩ በዘርፉ የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ከማሻሻሉም ባሻገር ግብዓቶችን በተገቢ መረጃ ላይ በመመስረት በፍትሃዊነት ለመጠቀም እና ውሳኔ ለመስጠት ያስችላሉ ብለዋል ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው አሁን ያለንበት ዘመን የዲጂታል መሆኑን ገልጸው እንደ ሃገር በርካታ ስራዎች መስራት እንደሚገባ አንስተው ዛሬ ከጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የለማው ሶፍት ዌር በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ እንደሚደረግ አስታውቀዋል ፡፡ በለማው ሶፍት ዌር ላይ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና አይቲ ክፍላ ባለሙያዎች ተጨማሪ ሃሳቦችን በመስጠት በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር በመድረኩ ተገልጿል ፡