
የሴቶች ልማት ህብረት መረጃን ዲጂታላይዝ በሆነ መልኩ ለማደራጀት የሚያስችል አዲስ ሲስተም ለምቶ ወደስራ እንዲገባ ከስምምነት ተደረሰ። ሲስተሙ የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከክልሉ ሰይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አንዲሁም ከጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር ያለመ ነው። በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር እንደገለፁት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃን መደራጀት የሴቶችና ህፃናትን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማጎልበት አበርክቶው ከፍተኛ ነው ብለዋል። የሴቶች ልማት ህብረት አጠቃላይ መረጃዎችን በየፈርጁ ለማስቀመጥ በሚያስችል መልኩ ያለመው ሲስተም ከመረጃ ጥረትና ከውጤታማነት አንፃር የሚያጋጥሙ ውስንነቶችን ለማረም አስቻይ ስለመሆኑም የቢሮ ኃላፊዋ ጠቁመዋል። ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊየን በላይ አባላት ያቀፈው የሴቶች ልማት ህብረት መረጃ አዲስ በለመው ሲስተም እንዲደራጅ የሚያስችል ስልጠና በየደረጃው በመስጠት በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል። የክልሉ ሰይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አንዲሁም የጉራጌ ዞን ሰይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የክልሉ ሰይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አንዲሁም የጉራጌ ዞን ሰይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በከፍተኛ ጥረት ሲስተሙን አልምተው ወደተግባር እንዲገባ ዝግጁ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በተቋሙ ስም አመስግነዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ሰላሙ አመዶ እንዳሉት በክልሉ ችግር ፈቺና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን አጋዥ የሆኑ በርካታ ሲስተሞች እያለሙ ወደስራ እንዲገቡ እየተደረገ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል። የክልሉን ሴቶችና ህፃናትን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሁሉም መስክ ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው የሴቶች ልማት ህብረት መረጃን ዲጂታላይዝ በሆነ መልኩ ለመደራጀት የተዘጋጀው ሲስተም አንዱ ነው ብለዋል። ሲስተሙ የሴቶች ልማት ህብረትን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር ጠቃሜታው ከፍተኛ ስለመሆኑ የጠቆሙት አቶ ሰላሙ ከመረጃ ጥረትና ፍጥነት ጋር ተያይዞ የሚጋጥሙ ውስንነቶችን የሚቀርፍ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የክልሉ ሰይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አንዲሁም የጉራጌ ዞን ሰይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር ማልማቱን አመላክተው ሲስተሙን በተሟላ መልኩ ወደተግባር ለማስገባት በሚደረገው እንቅስቃሴ አስፈላጊው ስልጠና በቅንጅት እንደሚሰጥም ገልጸዋል። አጠቃላይ ከሲስተሙ ማልማት፣ ጠቃሜታና መረጃ አሞላል ጋር በተያየዘ የጉራጌ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሲስተሙን ካለሙት በድኖች መካከል አንዱ የሆኑት ሄኖክ ወ/ጊዮርጊስ ለቢሮው አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት ገለፃ አድርገዋል። በገለፀው የሲስተሙ መልማት ለሴቶች ከለው ጠቀሜታ ዓላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ከሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት አንጻር በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላቱ በሰጡት አስተያየት የሲስተሙ መልማት ከሴቶች ልማት ህብረት መረጃ አደረጃጀት ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ጉድለቶችን በመቅረፍ ጥረት ያለውን መረጃ በዲጂታል መልኩ አዘምኖ በማደራጀት የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በእጅጉ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል። ከሲስተሙ ጋር በተያየዘ ከመረጃ አሞላልና አደረጃጀት ጋር በተገናኘ የተለያዩ ሀሳብና አስተያየት ለመድረኩ ቀርቦ ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ሲስተሙ ወደተግባር እንዲገባ በመግባባት ላይ ተደርሷል።