Skip to main content
zena34

ቢሮው ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር የሚያስችል ቅድመ-ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ። ወራቤ; መጋቢት 25/2017 ዓ/ም የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ባዩ-ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በቅንጅት እንሰት ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ ለማህበረሰቡ ለማሻጋገር በጋራ እየተሰራ እንዳለ ታወቀ፡፡ የእንሰት ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታና የሴቶችን የስራ ጫና የሚቀንስ በመሆኑ ከሚመለከታቸው የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ባለድርሻ ተቋማት ጋር ማስፈጸሚያ ዕቅድ በቅንጅት በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ለማስገባት የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ቴክኖሎጂውን በጉራጌ ዞን ቻሃ ወረዳ ለማሸጋገር የሚያስችሉ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች ማለትም የቦታ ልየታ ከመሰረተ-ልማት አኳያ፣ ሴቶችንና ወጣቶችን አደራጅቶ ከማዘጋጀት አንጻር እንዲሁም ሼድ ዝግጅት ስራዎችን በአካል በማየት መገምገም የተቻለ ሲሆን በቀጣይ የግንዛቤ ስልጠናዎች እና ቴክኖሎጂውን የማሸጋገር ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡