Admin2
Thu, 04/03/2025 - 10:09

ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሱፐርቪዥን ማካሄድ ጀመረ። ወራቤ: መጋቢት: 25/2017 ዓ/ም የሳይንስና ኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ ቢሮ በበጀት ዓመቱ የ9 ወራት ተግባራት አፈፃፀም በስር መዋቅሮች እስከ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ድርስ በመውረድ ሱፐርርቫይዝ የሚያደርግ ቡድን በማደራጀት ስምሪት ሰጥቷል። ሱፐርቪዥን ቡድኑ የሚያተኩረባቸው ነጥቦች በዋናነት ዲጂታላይዜሽን ትግበራን እና ችግር ፈቺ የኢኖቬሽንና ፈጠራ ስራ ውጤታማነትን መነሻ በማድረግ ምልከታ እያደረገ ይገኛል፡፡ ቡድኑ በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ፣ በቀቤና ልዩ ወረዳ ተግባራት ሱፐርቫይዝ ማድረግ ችሏል፡፡ በቀጣይ የሱፐርቪዥን ቡዱኑ በ9 ወራት የተከናወኑ ተግባራት በአካል ምልከታ በማድረግ የማረጋገጥ ስራ በመስራት ለየመዋቅሩ የፊት አመራር ግብረ መልስ እየሰጠ የሚቀጥል ይሆናል።