
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ እንደ ተቋም የመረጃ ስርዓቱን ለማዘመን እና ጊዜውን የዋጀ መረጃን ለማደራጀት ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመቀናጀት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። የካቲት ፦06/2017 ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በዛሬው ዕለት በወራቤ ከተማ በጋራ ግምገማ አድርጎል። ውይይት የተደረገባቸው የዳታቤዝ ስርዓቱን እና ዌብሳይቱን ለማልማት የተሻለ አስተዋፅዖ እንዳለው እና በዚህ ሂደት ውስጥ የተቋሙ የመረጃ ስርዓት የበለጠ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን። በተጨማሪም ኦንላይን ዕለታዊ የነዳጁ መረጃ ምዝገበ ስራዓት ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ስርዓቶችን ዲጂታላይዘሽን በማድረግ በንግድ ድርጅቶች እና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥ በአካል ይካሄድ ከነበረበት በይነ-መረብ በማሸጋገር በጣም ፈጠን ፣ወጪ ቆጣቢ እና ደህንነቱ አስተማማኝ እንዲሆን ከማድረጉም በተጨማሪ ወቅታዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወዳ ተቀናጀ ና አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ የሚደረግ ጉዞ እውን እንዲሆን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ወይም በማላመድና ነባር ቴክኖሎጂን በማሻሻል እና በአገልግሎት ላይ በማዋል ህብረተሰቡ ከዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ከተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር መስራቱ ወሳኝ እና አስፈላጊ መሆኑን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ ገልጸዋል ። በአጠቃላይ የተቋማት የመረጃ ስርዓት ማሻሻያ እና ለማስተዳደር የተደረጉ ስራዎች አዎንታዊ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆኑ ተመላክቷል።