
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን እና ጤና ቢሮ በቅንጅት ኢንስፔክሽን አደረገ!ኢንስፔክሽን የተካሄደባቸው ጤና ተቋማት ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ሀዲያ ዞን ንግስት እሌኒ ኮምፕርህንሲቭ ሆስፒታል፣ ከምባታ ዞን ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ ሆስፒታል እንዲሁም የስልጤ ዞን ወራቤ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ በኢንስፔክሽ የታዩ ህክምና መሳሪያዎች ኤክስሬይ ማሽን፣ ሲቲ ስካን ማሽን እና ኤምአራይ ማሽን ታይቷል። የኢንስፔክሽኑ ዓላማ ከጨረር አመንጪ መሳሪያዎች ከሚመነጭ ጨረር ህብረተሰቡን ለመከላከልና ደህንነቱን ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። ኢንስፔክሽኑ በዋናነት በጨረራ ክፍሎች ያሉ ምቹነት/ሴፍቲ/- ቅድመ ጥንቃቄ ጽሁፎች፣ አልባሳት፣ የጨረራ መለኪያ አጠቃቀምና ማስነበብ /TLD/፣ ላይ የተኮረ እንደሆነም የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙዲን ሁሴን ገልጿል። በኢንስፔክሽኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት የሙያ ፍቃድ፣ የስራ ፍቃድ፣ የጨረራ መጠንና ውሰድ፣ ግኝቶች ተገኝተዋል። በኢንስፔክሽኑ በአብዛኛው ሆስፒታሎች በጥንካሬ የታዩ መቀጠል ያለባቸው መልካም ስራዎች ታይተዋል ያሉት አቶ ሙዲን ሁሴን እንዲሁም በፍጥነት መታረም እና የእርምት እርምጃ በመውሰድ ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን ሆስፒታሎች በመጨረሻ ለሆስፒታሎቹ ማኔጅመንት አካላት ግብረ- መልስ መስጠት ተችሏል ብሏል፡፡