Skip to main content
zena16

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የጤና ተቋማት ስርጭት በጂኦስፓሻል ሳይንሳዊ ጥናት ማድረጉ ተሰማ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በጋራ በቅንጅት የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

 ኢንስቲትዩቱ በሀገር እና በክልል ደረጃ የጤና ተቋማት ስርጭት በጂኦ-ስፓሻል ዳታ ሳይንሳዊ ጥናት በማድረግ የተቋማት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ለሚደረግ ውሳኔ እና ቴክኖሎጂያዊ መፍትሔዎችን ለመስጠት እንደሚያስችል ጥናቱን ያቀረቡት ተመራማሪ አቶ እሱባለው ሙሉጌታ እና ተመራማሪ የኔዓለም አደራው በዝርዝር አቅረበዋል።

በመረኩ የተገኙት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኋላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን እና የክልሉ ጤና ቢሮ አካላት ጥናቱ በክልላችን የጤና ተቋማት ስርጭትና ተደራሽነት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሳይንሳዊ ስለሆነ ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም በቅንጅት ወደ ተግባር የሚገባ ሲሆን የሚመለከተቸው ባለድርሻ አካላት መተባበር እንደሚገባ ተገልጿል።