Skip to main content
zena2

ዘመኑን የዋጀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና ያላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች አቅም መገንባት ወሳኝ ነው፡- አቶ ከበደ ሻሜቦ ዘመኑን የዋጀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና ያላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትልና የኢኮቴ ልማት እና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ ገለፁ። ቢሮው በክልል ሴክተር መ/ቤቶች፣ በዞን እና በልዩ ወረዳ መዋቅሮች፣ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በሆሳዕና ቡታጅራ ሆስፒታሎች ለሚገኙ ኢኮቴ ባለሙያዎች በሲስተም ልማትና አስተዳደር ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ቴክኒካል ስልጠና በወራቤ ከተማ በሚገኘው አቶት ኢንተርናሽናል ሆቴል እየሰጠ ይገኛል። በስልጠናው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቢሮው ምክትልና የኢኮቴ ልማት እና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ ዘርፉ ከተጣለበት ኃላፊነት በመነሳት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል። አቶ ከበደ አያይዘው እንደገለፁት ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ ወደ ፊት እንዲራመድ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው።v ሶፍትዌር በማበልፀግ ፣ የዘርፉን ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የክህሎት ክፍተቶች በመሙላት፣ ወቅቱ የሚጠይቀውን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የሰው ሀይል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል። በሴክተሩ ትርጉም ያለው ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችለውን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል። ስልጠናው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚዘልቅ ሲሆን ከንድፈ ሀሳብ እስከ ተግባር ተኮር ቴክኒካል ስልጠና እንደሚሰጥም ተገልጿል።