Admin2
Thu, 11/05/2026 - 14:51
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከክልሉ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱም ቢሮው ለፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩቱ የሚሆን ሲስተምና ዘመናዊ ድህረ-ገጽ (Website) ለማልማት እንዲሁም በጋራ የምርምርና ቴክኖሎጂ ጥናት ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ወደ ትግበራ ለመግባት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በውይይት መድረክ ላይ አቶ ደምስ ገብሬ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ; ዶ/ር ንጉሴ አስረስ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።