Skip to main content
november 03 2026
"የምንመዘነው በሠራነው ሥራ ብዛት ሳይሆን ባመጣነው ለውጥና በዜጎች እርካታ ነው" — አቶ ደምስ ገብሬ
‎
‎"የምንመዘነው በሠራነው ሥራ ብዛት ሳይሆን ባመጣነው ለውጥና በዜጎች እርካታ ነው" ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ ገለፁ።
‎
‎ኃላፊው ይህንን ያሉት ቢሮው የበጀት ዓመቱን የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በሆሳዕና ከተማ በገመገመበት መድረክ ላይ ነው። ‎ቢሮው የግምገማ መድረኩን ያካሄደው ለታችኛው መዋቅር አመራሮችና ባለሙያዎች እየሰጠ ካለው የአቅም ግንባታ ስልጠና ጎን ለጎን ከመምሪያና ጽህፈት ቤቶች ጋር በመሆን ነው።
‎
‎በመድረኩም በክልሉ ሥር የሚገኙ መዋቅሮች የያለፉት ሦስት ወራት አፈጻጸም፣ ድጋፋዊ ክትትልና ግብረ መልስ እንዲሁም የ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያለበት ደረጃ ላይ ያተኮረ ሰፊ ግምገማ ተካሂዷል።
‎
‎ለክለሳው መነሻ የሚሆኑ ሰነዶች በቢሮው ከፍተኛ ባለሙያዎች እና በ"መሶብ" አንድ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚ የቀረቡ ሲሆን፣ የመምሪያና የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በቀረቡት ሰነዶች ላይ ተወያይተዋል። ኃላፊዎቹ በሩብ ዓመቱ የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
‎
‎በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሩ፤ የዲጂታል መንግሥት ግንባታን፣ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማትን፣ የመረጃ ደህንነትን እንዲሁም የኢኖቬሽንና የፈጠራ ሥራዎችን ማስፋፋት የጋራ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
‎
‎አክለውም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኃላፊነት የዘርፉ አመራር ብቻ ሳይሆን የመላው ተቋማት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመው፤ "የሚፈለገው በቦታው የተቀመጠ አመራር ሳይሆን ውጤት የሚያመጣ አመራር ነው፤ በሪፖርት ብቻ የሚታይ ስኬት ሳይሆን በተግባርና በዜጎች እርካታ የሚረጋገጥ ውጤት ያስፈልገናል" ሲሉ አሳስበዋል።
‎
‎ይህንን ተልዕኮ ለማሳካትም የክልሉ ቢሮ፣ የዞንና የልዩ ወረዳ መዋቅሮች በአንድ አቅጣጫና በተቀናጀ አሠራር ሊሠሩ እንደሚገባ አቶ ደምስ ገብሬ ተናግረዋል።