Admin2
Tue, 10/13/2026 - 10:43
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ማኔጅመንት በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይት አከናወነ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ማኔጅመንት በቀጣይ ትኩረት በሚሹ አቅጣጫዎችና ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ የተኮረ የውይይት መድረክ አካሂዷል። መድረኩ በቅርቡ በተካሄደው ክልል አቀፍ የአመራር መድረክ በተቀመጡ ውሳኔዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ተመስርቶ የተካሄደ ሲሆን በቢሮው የተጀመሩ የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚያስችሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የቢሮ ኋላፊ የሆኑት አቶ ደምስ ገብሬ ማቶከር እንደሚገባ አመላክተዋል።
በተጨማሪም በስብሰባው ላይ አዲስ ለተመደቡ አመራሮች ስለተቋሙ አጠቃላይ ሁኔታና አደረጃጀት ሰፊ ትውውቅና ገለፃ የተደረገ ሲሆን የስራ ርክክብም በይፋ ተፈፅሟል። በዚህ የውይይትና የርክክብ መድረክ ላይ የቢሮው የማኔጅመንት አባላት እና አዲስ የተመደቡ አመራሮች በሙሉ ተገኝተዋል።