Admin2
Fri, 10/16/2026 - 16:34
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ ማድረጊያ ቼክሊስት ገመገመ።
ወራቤ: ጥቅምት/2019 ዓ/ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀውን ቼክሊስት በመገምገም ለስራ አቅጣጫ ያስቀመጠበትን መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደገለጹት፤ የዚህ ክትትልና ድጋፍ ዋና ዓላማ የዝግጅት ምዕራፍና የተግባር አፈፃፀሞችን በጥንቃቄ በመፈተሽ ለቀጣይ የሥራ ጊዜያት የሚበጅ ጠንካራ ዐቅም መፍጠር ነው ብለዋል። አክለውም የስር መዋቅሮች በኢኖቬሽንና ዲጂታላይዜሽን ላይ ትኩረት በማድረግ፣ ተቋማዊ ለውጥና እድገት ማምጣት የሚያስችል ልዩ ዕቅድ አዘጋጅተው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በዚህ የግምገማና የውይይት መድረክ ላይ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት፣ ዳይሬክተሮች እንዲሁም የክትትልና ድጋፍ ቡድን አባላት ተሳታፊ ሆነዋል። በመጨረሻም ክትትልና ድጋፉ በማስፈፀሚያ ዕቅዱ እና ቢጋር መሠረት በጥብቅ ድስፕሊን መፈፀም እንደሚገባ ተመላክቷል።