Admin2
Thu, 08/20/2026 - 16:06
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የክረምት ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ስልጠና የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
ነሐሴ; 2018 ዓ/ም ወራቤ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለወጣቶች እያከናወነ የሚገኘውን የክረምት ስፔስ ሳይንስ; ጂኦስፓሻል; ኢንጂነሪንግና ሂሳብ ዙሪያ ስልጠና የክትትልና መስክ ምልከታ አካሄደ።
ምልከታው በወራቤ ከተማ በሚገኘው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል የተካሄደ ሲሆን፣ ልዩ ተስጥኦ ያላቸው ተማሪዎች በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል; ኢንጂነሪንግና ሂሳብ ዙሪያ ያገኙትን ሰፊ ተግባራዊ እውቀት ለመቃኘት ያለመ ነው።
በምልከታው የክረምት የበጎ ፍቃድ ስልጠናው ወጣቶች በዘመናዊው የጠፈርና ጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ ያላቸውን ክህሎት በማሳደግ ለወደፊት ፈጠራና ምርምር ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋል ሲሉ የቢሮ ም/ኋላፊ የሆኑት አቶ ሙሂዲን ሁሴን መልዕክት አስተላልፈዋል።
አክለውም በክልሉ ቢሮ፣ በዞኑ መምሪያዎች እና በወራቤ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል መካከል ያለው የተቀናጀ አሰራር ለስልጠናው ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።
በዚሁ የመስክ ምልከታ ፕሮግራም ላይ የቢሮ ኋላፊ አማካሪ አቶ ሁሴን ሳኒ; የሳይንስ ቴክኖሎጂ ዐቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አምደወርቅ ዘመዱ፣ የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹክራላህ አወል እንዲሁም የስልጤ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ጀሚላ ሁሴን የተገኙ ሲሆን፣ የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ለማበልፀግ የመስኩ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።