Skip to main content
zena 112
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የወራቤ መሶብ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል እና የወራቤ የወንዝ ደር ፓርክን ጎበኙ
የቢሮው አመራሮችና መላው ሰራተኞች ባደረጉት ጉብኝት በማዕከሉ ስራ አስኪያጅና ባለሙያዎች እንዲሁም በፓርኩ ኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
በማዕከሉ የቀለጠፈ አገልግሎት በአንድ ቦታ በተቀናጀ ሁኔታ እየሰጠ እንደሚገኝ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዲኑ መሀመድ አስረድተዋል።
በክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር የተመራ አመራርና ባለሙያ የማዕከሉን አጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ የጎበኘ ሲሆን ማዕከሉ እየሰጠ ያለው አገልግሎት የሚደነቅና ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት እንደሆነም የቢሮ ኃላፊዋ ገልፀዋል።
የጉብኝቱ ዋና አላማ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች የተከናወኑ ማራኪ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት በተናቀቀ ሁኔታ የ2019 የስራ ዘመንን እንዲጀምሩ ለማድረግ ስለመሆኑም ወ/ሮ ዘቢባ አመላክተዋል።
በክልሉ የተገነቡት የአንድ ማዕከሎች እና ፓርኮች እጅግ የሚደናቁና ክልሉን የተሞክሮ ማዕከል የሚያደርጉ አመርቂ ስራዎች ናቸው ብለዋል።
የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በወራቤ የወንዝ ደር ፓርክ ውስጥ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።