Skip to main content
july 28 2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ እና የክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በጋራ በመሆን በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀል አምባ ከተማ በ2018 በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ የመከላከያ ሰራዊት ተመላሽ አባል ቤት ግንባታ አስጀመሩ። ‎ ‎

ሀምሌ 21/2018(ወልቂጤ) ‎ ‎ የክልሉ ተቋማት በጋራ በመሆን በወረዳው መሀል አምባ ከተማ በ2018 በክረምት በጎ ፈቃድ የወታደር አህመኑር ጀማል የቤት ግንባታ አስጀምረዋል። ‎ ‎የክልሉ መንግስት በዞኑ በተለያዩ የወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የክረምት በጎ ፍቃድ ተግባራት አጠናክሮ መቀጠሉን ተመላክቷል። ‎ ‎ለሀገር ህይወታቸውና አካላቸውን የሚሰጡ የመከላከያ አባላት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ሀገርን የማላቅና ለተጎጂዎችም እውቅናም የመስጠት ጉዳይ ነው። ‎ ‎

ከቤት ግንባታ ጎን ለጎን በመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። ‎ ‎በፕሮግራሙም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ፣ የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ፣ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ፣ የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ፣ የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን፣ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።